LIKTERA
ጥርስ የገባች ሀገር
ጥርስ የገባች ሀገር
Low stock: 2 left
Couldn't load pickup availability
ግብፅ አፄ ሀይለስላሴን ለመግደል ያረገችው ሙከራ
የ1945ቱ የፓሪስ የሰላም ስብሰባ ላይ ኢትዮጵያ የኤርትራን የይገባኛል ጥያቄ ስታቀርብ, ግብፅ ተቃወመች::
ይሄንን ሁላችንም የኢትዮጵያ ልኡካን ጠብቀነው ስለነበር ብዙም አልደነገጥንም:: ነገር ግን ግብፅ ከዚህ በላይ የራሷን የቅኝ ግዛት አላማ ነድፋ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ፈፅሞ አላወቅንም ነበር::
የፓሪሱን ስብሰባ እንደጨረስን በማግስቱ ግን ግብፅ የአባይ ሸለቆ ህብረት የሚል በአባይ ዙሪያ ያሉትን የአፍሪካ ሀገራት ቅኝ ለመግዛት ፕላን አውጥታ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ ሰማን::
ይሄንን የሰማነው ሱዳንን ከእንግሊዞች እጅ ለመቀበል ድርድር ላይ ናት የሚለውን ወሬ ለማጣራት ስንሞክር ነበር::
በሚያዚያ ወር 1947 ፋሩቅ በአፄ ሀይለስላሴ ላይ ግድያ እፈፅማለሁ እንዳለ መረጃው ደረሰን:: ይሄ ወሬ እንደተሰማ ወዲያው የአሜሪካ 2 መኮንኖች ወደኢትዮጵያ መጡ::
ነገር ግን የመግደል ሙከራው እንደማይሳካለት ሲያውቅ የአባይን ጉዳይ ከስጋት ለማዳን የሚቻለው በውሀው ዙሪያ ያሉትን ሀገራት በቅኝ ግዛት ስናውል ብቻ ነው የሚል ፅኑ አቋም ይዞ እየሰራ መሆኑ ተሰማ::
ግብፅ በእቅዷ መሰረት ኢትዮጵያን, ኤርትራን,ኬኒያን,ዩጋምዳን እንዲሁም የእንግሊዝ, የፈረንሳይ እና የጣልያን ሱማሌላንዶችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የእየሰራች መሆኑ ለሀይለስላሴ መንግስት መረጃው ደረሰ::
ይሄ ፕሮጄክት በ1952 የፋሩቅ መንግስት በናስር መንግስት ሲተካም ተጠናክሮ ቀጥሎ ነበር::
በፕሮጄክቷም መሰረት ኢትዮጵያን ለማዳከም ታላቋ ሶማልያን እንመሰረታለን ብለው የተነሱትን ሶማሊዎች ማስታጠቅ ጀመረች::
አፄ ሀይለስላሴ ግን የእራስቸውን ሀይል እስከሚያደራጁ ድረስ ምንም መልስ ሳይሰጡ እያለሳለሱ ታግሰው ዝም አሉ::
ወደያው የምድር ባቡሩ በፈረንሳዩች እንዲንቀሳቀስ እና የንግዱ እንቅስቃሴ ቶሎ እንዲፋጠን ተደረገ::
በሁዋላ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ሀይል እየበረታ ሲመጣ የቅኝ ግዛት እቅዷንም ሳትጀምረው ቀረች::
ምስጋና: ለፀሀፊ John H. Spencer( ነፍስህን በገነት ያኑረው)
ምንጭ መፅሀፍ: ጥርስ የገባች ሀገር(Ethiopia at bay)
ካነበብኩት ላይ ያካፈልኳችሁ እኔ አፈወርቅ ነኝ ይቆየን::
Taken from the book
Book by John H. Spencer
Translated by Mengistu Hailemariam Araya
& Mezgebe Biraka Beleleng
Book Condition: VG- clean copy only minor shades
Share
